Gubae

አንተ ግን ያው አንተ ነህ

Ante Gin Yaw Ante Neh

አገኝሁ ይደግ · እጣዬ · 1992

አንተ ግን ያው አንተ ነህ 2x ፍቅር ከበረዶ ቀዝቅዞ ወንድም ወንድሙን ሲርቀው አዳራሽዋ ፈርሶ ትህትና ትዕቢት መዝጊያዋን ሲያወልቀው ፅድቅህ ከወለል ላይ ወድቆ በሀጥያት ጫማ ቢረገጥ ሀሰት ዙፋን ዘርግቶ በ እውነቶች ሲላገጥ ግዛትህ አያበቃም ወሰንህ አይለካም ሁሉን አሳልፈህ ዘላለም ትኖራለህ አንተ ግን ያው አንተ ነህ 2x ባለጠጋ ነኝ ብሎ ቤቱን ከሰማይ ጥግ ቢሰራ ደረጃ መሰላሉ በዝቶ ቢወጣ ላይኛው ተራራ በገመድ ተጎትቶ ሲወርድ አዳራሹ ስትፈርስ መመኪያው አንተ ግን ፀንተህ ትኖራለህ የሰው ልጅ ሚዛኑ መለኪያው ግዛትህ አያበቃም ወሰንህ አይለካም ሁሉን አሳልፈህ ዘላለም ትኖራለህ አንተ ግን ያው አንተ ነህ 2x ድሀ ከፋንድያ ተነስቶ በክብር ስፍራ ላይ ቢቀመጥ ቃሉ እንደ ንጉስ ቃል ሆኖ በሸንጎ ስብሰባ ቢደመጥ ሰው ከነበረበት ጨለማ በወንጌል ብርሃን ሲላቀቅ በደለኛ መሆኑ ገብቶት ተፀፅቶ ካንተ ሲታረቅ ግዛትህ አያበቃም ወሰንህ አይለካም ሁሉን አሳልፈህ ዘላለም ትኖራለህ አንተ ግን ያው አንተ ነህ 2x ተውልድ ይሄዳል ይመጣል ነገስታትም ይፈልሳሉ የማለዳዋቹ ተረስተው አፋላዎች ይወደሳሉ አሀዱ የለህ ማክተሚያ አመታትህም አያልቅም ዘላለም ከብረህ ትኖራለህ ፍጥረታት ቢያውቁህ ባያውቁህ

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች