Gubae

አልረሳም

Alresam

አገኝሁ ይደግ · እጣዬ · 2003

[Chorus] አልረሳም አልረሳም አልረሳም የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን ጌታ የባረከኝን ከ ትቢያ ያነሳኝን እንዴት እረሳለሁ አስታውሰዋለሁ እንዴት እረሳለሁ ጌታን አከብራለሁ [Bridge] [Verse 1] ዙሪያው ገደል ሆኖ መውጫ አጥቼ ከምስጋና ህይወት ተለይቼ ግን እግዚአብሔር በጣም አዘነ እንደገና አቆመኝ በአዲስ ጉልበት [Chorus] አልረሳም አልረሳም አልረሳም የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን ጌታ የባረከኝን ከ ትቢያ ያነሳኝን እንዴት እረሳለሁ አስታውሰዋለሁ እንዴት እረሳለሁ ጌታን አከብራለሁ [Verse 2] ነፍሴን እጅግ ተርባ ተጠምታብኝ ቀኑ እንደ እረፍት ሲሆንብኝ የሰማይን መስኮት ከፈተና ጓዳዬን ሞላልኝ በምስጋና [Chorus] አልረሳም አልረሳም አልረሳም የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን ጌታ የባረከኝን ከ ትቢያ ያነሳኝን እንዴት እረሳለሁ አስታውሰዋለሁ እንዴት እረሳለሁ ጌታን አከብራለሁ [Instrumental] [Verse 3] የመከራው ሌሊት ምንው በዛ እግዚአብሔር ዝም አለኝ እንደዋዛ ብዬ ነበር ግን ጌታ አይጥልም ሰምቶ ይመልሳል ዝም አይልም [Chorus] አልረሳም አልረሳም አልረሳም የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን ጌታ የባረከኝን ከ ትቢያ ያነሳኝን እንዴት እረሳለሁ አስታውሰዋለሁ እንዴት እረሳለሁ ጌታን አከብራለሁ [Verse 4] ዕሰይ ሜዳ ሆነ ያ ተራራ ሌሊቱ አልፎ ጨለማዬ በራ የረዳኝም ጌታ እባርከዋለሁ በጉባኤ መሃል አዜምለታለሁ [Chorus] አልረሳም አልረሳም አልረሳም የትላንቱን የቀድሞውን የጠዋቱን ጌታ የባረከኝን ከ ትቢያ ያነሳኝን እንዴት እረሳለሁ አስታውሰዋለሁ እንዴት እረሳለሁ ጌታን አከብራለሁ [Instrumental]

አገኝሁ ይደግ · ሁሉም ዘማሪዎች