Gubae

ምን ደላው ለእርሱ

Men Delaw Lersu

አዲሱ ወርቁ · የመስቀሉ ፍቅር · 2006

ልደቱ ፡ በረት ፡ ሞቱ ፡ በመከራ ፡ እንጨት ፡ ላይ ዕድሜውን ፡ ፈጅቶ ፡ በስቃይ ለማልጠቅመው ፡ ለእኔ ፡ ጌታ ፡ እራሱን ፡ ጐዳ ፍርድ ፡ ተሸክሞ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ተነዳ አዝ፦ ምን ፡ ደላው ፡ ለእርሱ ፡ ምን ፡ ደስ ፡ አሰኘው የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ እንደምን ፡ ማቀቀው አዬ ፡ ፍቅር ፡ ሆኖ ፡ ሞተ ፡ እንደተገፋ የእሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኖ ፡ አለ ፡ አንገቱ ፡ ደፋ (፪x) ፍቅርን ፡ ለብሶ ፡ ርህራሄ ፡ አስገድዶት የነፍሴ ፡ ለቅሶ ፡ ተሰምቶት መጣ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሞተ ፡ ተጐሳቁሎ የአባቱን ፡ ፍቃድ ፡ ፈጽሞታል ፡ ታግሎ አዝ፦ ምን ፡ ደላው ፡ ለእርሱ ፡ ምን ፡ ደስ ፡ አሰኘው የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ እንደምን ፡ ማቀቀው አዬ ፡ ፍቅር ፡ ሆኖ ፡ ሞተ ፡ እንደተገፋ የእሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኖ ፡ አለ ፡ አንገቱ ፡ ደፋ (፪x) ምን ፡ ዋልኩለት ፡ ለእዚህ ፡ ወዳጅ ፡ ከቶ ለሞተው ፡ እኔን ፡ ተክቶ አልተገራም ፡ ልቤ ፡ አልታረቀም ፡ ገና መቼም ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥ ፡ ቀን ፡ ይመጣልና አዝ፦ ምን ፡ ደላው ፡ ለእርሱ ፡ ምን ፡ ደስ ፡ አሰኘው የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ እንደምን ፡ ማቀቀው አዬ ፡ ፍቅር ፡ ሆኖ ፡ ሞተ ፡ እንደተገፋ የእሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኖ ፡ አለ ፡ አንገቱ ፡ ደፋ (፪x)

አዲሱ ወርቁ · ሁሉም ዘማሪዎች