Gubae

ከሞትም ያድናል

Kemotem Yadenal

አዲሱ ወርቁ · የመስቀሉ ፍቅር · 2006

ርዕስ ከሞትም ያድናል ዘማሪ አዲሱ ወርቁ Volume 1 አልበም ክቡር ክቡር በሞት ጥላ የሚያድር በግዞች ሸለቆ ጠላት የሚመታው አሸምቆ ከአንበሳው መንጋጋ ለጣር የተጣለ ነበር ወገኔ የቆሰለ አዝ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፪x) ጌታ ደርሶለታል ወንጌል ልኮለታል ሰማያዊው ብርሃን በርቶለታል መልዕክተኞች ወጡ ጠላትን ገጠሙ በመስቀሉ ጉልበት ድል አደረጉት አዝ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፪x) ዓለምና ትርፏን ወደ ኋላ ገፍቶ ከመታወቅ ይልቅ መናቅ መርጦ ዘሩን ተሸክሞ በለቅሶ የሚዘራ በደስታ ያጭዳል ከአምላክ ጋራ አዝ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (፬x)

አዲሱ ወርቁ · ሁሉም ዘማሪዎች