Gubae

ጌታዬን አከብርሃለው

Gietayien Akebralehu

አዲሱ ወርቁ · የመስቀሉ ፍቅር · 2006

አነባ ፡ ጌታዬ ፡ አፈር ፡ ላይ ፡ ተደፍቶ የወደቀበትን ፡ ጭንቀት ፡ ተመልክቶ ጌታዬ ፡ ተጨንቆ ፡ አባዬ ፡ ሆይ ፡ አለ አጋዥ ፡ አልተገኘም ፡ ለጌታ ፡ የዋለ መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ትከሻው ፡ ተላጠ ግርፋቱ ፡ በዛ ፡ ገላዉ ፡ ተመለጠ ራቁቱን ፡ ደም ፡ ሲያፈስ ፡ በቀራንዮ ፡ ዋለ አንገቱ ፡ ደፋ ፡ ሲል ፡ ዕዳ ፡ ተከፈለ አዝ፦ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ዝናን ፡ ከበሬታን ፡ ሞገስን ፡ በሥጋ ሊያገኝ ፡ ወዶ ፡ ነፍሱን ፡ ከዓለም ፡ ከሚያስጠጋ ይሻላል ፡ ጭጋፉ ፡ ውዳቄን ፡ እኔን፡ መሳይ በሥጋው ፡ ተንቆ ፡ በእምነት ፡ ጌታን ፡ የሚያይ አዝ፦ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ማቆ ፡ በመከራ ፡ ጐስቋላ ፡ አካል ፡ ይዞ በረሃን ፡ የሚዘልቅ ፡ ጌታን ፡ ተመርኩዞ ተሸማቆ ፡ ኑሮውን ፡ ለጌታ ፡ ሲል ፡ ችሎ ያለፈን ፡ አየሁት ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ አዝ፦ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ በሞቱ ፡ ሊመስለዉ ፡ ጌታን ፡ ተከትሎ ወድቆም ፡ የሚነሳ ፡ አልሸነፍ ፡ ብሎ ለጠላቱ ፡ ታግሎ ፡ የማታ ፡ የማታ ጌታው ፡ ምሎለታል ፡ እርሱ ፡ እንደሚረታ አዝ፦ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ ጌታዬን ፡ አከብራለሁ (፫x) ፡ በኑሮዬ

አዲሱ ወርቁ · ሁሉም ዘማሪዎች