Gubae

ሲወድ ጌታ

Siwed Gieta

አዲስዓለም አሰፋ · ሰባሪው ጌታ ከፊቴ ወጥቷል · 2008

ነፍስ ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ በዘላለም ፡ መውደድ ፡ ወዶኛል (፪x) ፍቅሩ ፡ ይቀንሳል ፡ ብዬ አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል አልሰጋም በዚህ ደስ ይለኛል (፪x) አዝ፦ ለዘላለም ነዉ (፬x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ እስከመስቀል ፡ ነዉ (፪x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ ላይጠላ ፡ ነዉ (፪x) እኩል ፡ ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ፍቅሩ ፡ እኩል አቅቶኛል ፡ ብሎ ፡ ሸርተት ፡ አይል ባስቀመትኩት ፡ ቦታ ፡ የሚገኝ ታማኝ ፡ መልካም ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ ያለኝ ነፍስ ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ በዘላለም ፡ መውደድ ፡ ወዶኛል (፪x) ፍቅሩ ፡ ይቀንሳል ፡ ብዬ አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፪x) አዝ፦ ለዘላለም ፡ ነዉ (፬x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ እስከመስቀል ፡ ነዉ (፪x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ ላይጠላ ፡ ነዉ (፪x) እስከመጨረሻ ፡ ወዶኛል ፡ ወዶኛል በማይለቀው ፡ እጁ ፡ ይዞኛል ፡ ይዞኛል ከቅፎቹ ፡ መሃል ፡ አድራለሁ ፡ አድራለሁ ፍቅሩ ፡ እያባበለኝ ፡ ኖራለሁ ፡ ኖራለሁ ዛሬ ፡ ይዞ ፡ ነገ ፡ አይተወኝም ፡ ሂጂ ፡ ብሎ ፡ አያባርረኝም ተመችቶኝ ፡ ኖራለሁ ፡ በቤቱ ፡ ተሸክሞኝ ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ ዛሬ ፡ ይዞ ፡ ነገ ፡ አይለቀኝም ፡ ሂጂ ፡ ብሎ ፡ አያባርረኝም ያለፍርሃት፡ ኖራለሁ ፡ በቤቱ ፡ ተሸክሞኝ ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ ነፍስ ፡ እስከመስጠት ፡ ድረስ በዘላለም ፡ መውደድ ፡ ወዶኛል (፪x) ፍቅሩ ፡ ይቀንሳል ፡ ብዬ አልሰጋም ፡ በዚህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፪x) አዝ፦ ለዘላለም ፡ ነዉ (፬x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ እስከመስቀል ፡ ነዉ (፪x) ሲወድ ፡ ጌታ ፡ ላይጠላ ፡ ነዉ (፪x) እስከመጨረሻ ፡ ወዶኛል ፡ ወዶኛል በማይለቀው ፡ እጁ ፡ ይዞኛል ፡ ይዞኛል ከቅፎቹ ፡ መሃል ፡ አድራለሁ ፡ አድራለሁ ፍቅሩ ፡ እያባበለኝ ፡ ኖራለሁ ፡ ኖራለሁ

አዲስዓለም አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች