Gubae

ከአንተ ወዴት

Kante Wedet

አዲስዓለም አሰፋ · ጆሮዬን ልብሳ · 2018

ካንተ ወዴት እሄዳለው ካንተ ወደ ማን እሄዳለው 2x የሱስ ህይወቴን አድነህ ባንተ መሞት ሰው ሆኛለሁ ከጥላህ በታች አርፌ ፍቅርህን ቀምሼዋለሁ 2x አመሰግንሃለሁ 4x ምስጋናዬ ስምህን ያክብረው እልልታዬ ማደሪያህን ይሙላው 2x የምትበላ የህይወት እንጀራ ድኜ ቀረሁኝ ስምህን ስጠራ 2x ሮጬ አመለጥኩኝ ከመከራዬ ልዘምር መጣሁ ተከፍሎ ዕዳዬ ልዘምር መጣሁ ታብሶ ዕምባዬ አዝ፦ እስትንፋሴ የመኖሬ ህልውና አንተኮ ነህ የቤቴ ራስ ገናና ዝና ክብሬ ደም ግባቴ ሞገሴ ይኸው መጣሁ ልሰግድልህ እየሱሴ እንካ ክብሬን እንካ አምልኮዬን የሚገባው ላንተ ነው ሰው ያደረገኝ ደምህ/ልጅህ ነው 2x በመስቀል ጣርህ የወለድከኝ ከሲዖል ነጥቀህ ያወጣኸኝ 2x የልቤን ኃጥያት የተወክልኝ በብዙ ምህረት የከበብከኝ በጥንቃቄ ያሳደከኝ አዝ፦ እስትንፋሴ የመኖሬ ህልውና አንተኮ ነህ የቤቴ ራስ ገናና ዝና ክብሬ ደም ግባቴ ሞገሴ ይኸው መጣሁ ልሰግድልህ እየሱሴ እንካ ክብሬን እንካ አምልኮዬን የሚገባው ላንተ ነው ሰው ያደረገኝ ደምህ/ልጅህ ነው 2x ካንተ ወዴት እሄዳለው ካንተ ወደ ማን እሄዳለው 2x የሱስ ህይወቴን አድነህ ባንተ መሞት ሰው ሆኛለሁ ከጥላህ በታች አርፌ ፍቅርህን ቀምሼዋለሁ 2x

አዲስዓለም አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች