Gubae

ጆሮዬን ልብሳ

Joreyen Libesa

አዲስዓለም አሰፋ · ጆሮዬን ልብሳ · 2018

ሃጥያት ፡ አላገኘህም ስንፍና ፡ አልከሰሰህም ስትገዛ ፡ አልደከመህም እርጅና ፡ አላወቀህም(፪) እኔም ፡ አላውቅህም ፡ የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም(፪) እኔም ፡ አላውቅህም ፡ የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም(፪) የለህም ፡ እኩያ የለህም ፡ አምሳያ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ(፪) ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ(፬) የነገሥታት ፡ ወገብ ፡ ትጥቅ ፡ የምታስፈታ ሓያል ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ(፫) የፍጥረት ፡ መገኛ ፡ ሕያው ፡ መሠረት አትሰላ ፡ በዓመታት ፡ አትደመር ፡ በዘመናት አትሰላ ፡ በዓመታት የትኛውም ፡ ምሑር ፡ ሒሳብ ፡ አይሰራህም የትኛውም ፡ ሰዓሊ ፡ ብሩሽ ፡ አይቀባህም የቱም ፡ አንጠረኛ ፡ ቀርጾ ፡ አያወጣህም አሐዱ ፡ አትባልም ፡ ደረጃም ፡ የለህም ኧረ ፡ እኔስ ፡ ለክብርህ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ለዝናህ ሽርጉድ ፡ ልበል ፡ ላገልግልህ ጆሮዬን ፡ ልብሳ ፡ ልኑልርህ(፪) ልኑርልህ(፬) እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሞትን ፡ አሸነፈ እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ጨለማ ፡ ገፈፈ እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ዙፋንህ ፡ የጸና ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና ዙፋንህ ፡ የጸና (፪x)

አዲስዓለም አሰፋ · ሁሉም ዘማሪዎች