Gubae

መዝሙረ ዳዊት 134

Psalms 134 · የ1954 አማርኛ · 3 ቁጥሮች

1እነሆ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዬች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ።

2በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም ባርኩ።

3ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።